Skip to main content
 

ስለ እኛ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በሞንትሪያል በመደበኛ አምልኮ፣ በቅዱሳት ምስጢራት እና በወንጌል ትምህርቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን መንፈሳዊ አስተምህሮት እና ሥርዐቶችን ለመጠበቅ የተቋቋመና በዚህ ዙርያ በቁርጠኛነት እየሰራ ያለ ቤተክርስቲያን ነው። ከሃይማኖታዊ አገልግሎቶቻችን ባለፈ፣ የማህበረሰባችንን ቅርስ ለመጠበቅና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ እና እሴቶችን የሚያከብሩ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ለምዕመኑ እንደ ባህላዊ እና ትምህርታዊ ሰንሰለት ሆኖ ያገለግላል። አንዳችን ሌላውን እንድንወድ በታዘዝነው መንፈሳዊ ትዕዛዝ መሰረት፤ ማንኛውንም የአድልዎ እና የጭፍን ጥላቻ ስሜቶችን እና አሰራሮችን በጽኑ በመቃወም፣ ሰላምን እና ማህበረሰባዊ መደጋገፍን የሚያበረታታ፣ ሁሉንም የሚያካትት አካባቢ ለመፍጠር የተቻለውን ሁሉ የምናደርግ ነን።

መደበኛ የአገልግሎት ሰዓታት

ረቡዕ

ጠዋት ከ፩ - ፯ ሰዓት

(8:00 AM - 1:00 PM)

ቅዳሜ

፰ - ፲፩ ሰዓት

(2:00 PM - 5:00 PM)

እሁድ

ጠዋት ከ፩ - ፯ ሰዓት

(7:00 AM - 1:00 PM)

ያግኙን